online web builder

የበጎ አድራጎት ጽ/ቤታችን በየዓመቱ ለአቅመ ደካሞች እና ችግረኛ ቤተሰቦች ጾም የማስፈሰክ እና የዓይነት ድጋፍ ከምዕመናን እንዲሁም በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ ያሉ በጎ አድራጊዎችን በማስተባበር በበአላት በአስደሳች ሁኔታ የበጎ አድራጎት ስራዎችን ያከናውናል። ሁልግዜም በየአመቱ የገና እና የፋሲካ በአል የነዳያን ጾም ማስፈሰኪያ መርሐ ግብሮች ላይ ዓላማውን የጠበቀ የማስፈሰክ መርሐ ግብር እንዲሆን እና ተደራሽቱ ለተቸገሩ ነዳያን፣ ጎዳና ተዳዳሪዎች እና ጸበልተኞች እንዲሆን እንዲሁም በበጎ አድራጎቱ ስር ያሉ ከ30 በላይ በቤታቸው ሆነው በአቅም ውስንነት ምክንያት በአልን ማሳለፍ ላቃታቸው ነገር ግን ወጥተው መለመን ለከበዳቸው ሰዎችም እንዲሁ በአሉን ከልጆቻቸው ጋር በደስታ የሚያከብሩበትን ዶሮ፣ ስጋ፣ ዱቄት፣ ዘይት፣ ሽንኩርት፣ እንቁላል፣ ሎሚ፣ እንጀራ እና የጎደላቸውን ነገር እንዲገዙበትም ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ ይደረጋል። 

© Copyright 2024 Finot Charity - All Rights Reserved