how to make a website for free

ሌላው በበጎ አድራጎታችን በትኩረት የምንሰራበት ድጋፍ ለሀጻናት የትምሕርት አቀፍ እርዳታዎች ናቸው። በዚህም ስር የሚካተቱ የበጎ አድራጎት ሰራዎች

  1. በመስከረም ወር ለተማሪዎች የበጎ አድራጎቱ የተለያዩ በጎ አድራጊ ሰዎችን በማስተባበር ተቋሙ በቋሚነት ለሚያስተምራቸው ከ36 በላይ ለሆኑ የትምህርት መማሪያ ቁሳቁስ ለሌላቸው ተማሪዎች እገዛ ይደረጋል። በዚህም ከበጎ አድራጊዎች በገንዘብ እና በአይነት በሚሰበሰብ የስፖንሰርሺፕ እርዳታ በጠቅላላ ለተቸገሩ ተማሪዎች የ(ቦርሳ፣ ጫማ፣ ደብተር፣ እስኪሪብቶ፣ እርሳስ፣ ላጲስ፣ መቅረጫ) ድጋፍ በየአመቱ ያደርጋል።
  2. እንዲሁም በቋሚነት በሳምንት ለአራት ቀናት እነዚህን ተማሪዎች እና ሌሎች በትምህርታቸው ደከም ያሉ ተማሪዎችን በመሰብሰብ እና አስጠኚ በጎ ፍቃደኞችን በማስተባበር የቀለም ትምህርት እያስጠናን በቅርበት የትምህርት ሁኔታቸውን እየተከታተልን እንገኛለን።
  3. ለተማሪዎች ማስጠኚያ የሚሆኑ እና ወስደው እንዲያነቡባቸው የታሰቡ የተለያዩ መጻህፍትንም በመሰብሰብ ለልጆቹ እንዲያነቡ ይሰጣል።
  4. ለተማሪዎቹ የስነ ልቦና እርዳታም በማድረግ ከት/ት ባሻገርም ያላቸውን እምቅ ሃይል እንዲያወጡ ለማድረግ ጥረት ይደረጋል።

© Copyright 2024 Finot Charity - All Rights Reserved