የበጎ አድራጎት ጽ/ቤታችን በአመት ውስጥ በተመረጡ ግዜያት ለነዳያን፣ ለጎዳና ተዳዳሪዎች እና ችግረኛ ቤተሰቦች የአልባሳት ድጋፍ ከምዕመናን እና ከበጎ አድራጊ ሰዎች በማስተባበር የበጎ አድራጎት ስራን ውጤታማ በሆነ ሁኔታ ያከናውናል። በአመት ከሶስት ግዜ ባላነሰ የአልባሳት ድጋፉን ለማድረግ በቅጽረ ቤ/ክ ውስጥ እና ውጪም በጎ አድራጊዎችን በማስተባበር አልባሳትን ይሰበስባል። ያሰባሰበውንም ልብስ ለመለገስ በሚመች መልኩ በጾታ እና በእድሜ በመከፋፈል ታሽጎ ከተዘጋጀ በኋላ በተመረጠው ቀን አጥቢያው ላይ ያሉ ነዳያን በሙሉ እንዲገኙ በመጥራት የአልባሳት ድጋፉ ስርዓትን በጠበቀ መልኩ ይካሄዳል።
እንዲሁም ሌሎች ሙሉ በሙሉ ፈጻሜ ያላገኙ የበጎ አድራጎት ስራዎች ለምሳሌ ለተለያዩ ድጋፍ ለሚፈለጉ ሰንበት ተማሪዎች እና የተቸገሩ ሰዎች የስኮላርሺፕ ስልጠና እድሎችን ለማመቻቸት ጥረቶች የተደረጉ ሲሆን ፍጻሚያቸው ወይም ውጤታቸው እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በመጪው ግዜያት የሚታይ ይሆናል።